ሁለት ዓይነት የስደተኞች ችሎቶች አሉ፡ ምናባዊ (ኦንላየን ላይ) እና በአካል ናቸው።
ምናባዊ ችሎቶች
ምናባዊ ችሎት በመስመር ላይ [ኦንላየን] ይካሄዳል። ሁሉም ሰው የማይክሮሶፍት ቡድኖችን በመጠቀም በኮምፒዩተር ስክሪን ላይ ይታያል።
ለምናባዊ ችሎትዎ መዘጋጀት
እርስዎ ወይም የህግ ተወካይዎ IRB-RPD ቀን እና ሰዓት ካስቀመጠ በኋላ የመቅረብያ/የመገኘት ማሳወቂያ ደብዳቤ ይደርስዎታል። ይህንን ማስታወቂያ በጥንቃቄ ያንብቡ፣ ምክንያቱም ለምናባዊ ችሎት ምን ማድረግ እንዳለበት ስለሚያብራራ።
ምናባዊ ችሎት ሲቀርቡ ሊኖርዎት የሚገባ ነገረ፣
- አስተማማኝ፣ ደህንነቱን የተጠበቀና ከፍተኛ ፍጥነት ያለው በይነመረብ/ኢንተርኔት
- ኮምፒተር ወይም አነስ ያለች ኮምፒተር/ ታብሌት
- ፀጥ ያለና ጥሩ የግል ቦታ
የህግ ተወካይ ካልዎት ለችሎቱ ወደ ቢሮአቸው መሄድ ይችላሉ። ይህንን ከህጋዊ ተወካይዎ ጋር ይወያዩ።
ወደ ህጋዊ ተወካይዎ ቢሮ የማይሄዱ ከሆነ፣ ምናባዊ ችሎቱን ለመስራት የሚያስፈልግዎ ነገር እንዳለዎት ያረጋግጡ። ኮምፒውተር ወይም ታብሌት ወይም ኢንተርኔት ከሌልዎት ከIRB-RPD እርዳታ ይጠይቁ። የIRB-RPD ኮምፒውተር ወይም ታብሌቶች/የእጅ ኮምፒውተሮች በቢሯቸው በአካል ተገኝተው መጠቀም ይችላሉ። በክልልዎ IRB-RPD በስልክ፣ በኢሜል ወይም በፖስታ ይጠይቁ። ችሎት ከመቅረብዎ በፊት ቢያንስ ከአስር የስራ ቀናት በፊት እነሱን ማነጋገር አለብዎት።
ከችሎቱ አምስት ቀናት ቀደም ብሎ፣ IRB-RPD ለህግ ተወካይዎን የቪዲዮ ኮንፈረንሱን መጋነኛ መስመር/ሊንክ ይልካል። ይህን መጋነኛ መስመር/ሊንክ ከእርስዎ ጋር ይጋራሉ። ምንም አይነት ህጋዊ ተወካይ ከሌልዎት፣ IRB-RPD የመጋነኛ መሰመሩን/ሊንኩን በኢሜል ለራስዎ ይልክልዎታል። IRB-RPD የእርስዎ ትክክለኛ ኢሜይል አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር እና የፖስታ አድራሻ እንዳለው ያረጋግጡ።
በምናባዊ ችሎትዎ ላይ
በምናባዊ ችሎትዎ ቀን ችሎቱ መሰማት ከመጀመሩ 15 ደቂቃዎች በፊት በመጋነኛ መስመር ላይ ስብሰባ እንዲቀላቀሉ ይጠየቃሉ። ይህ የበይነመረብ ግንኙነትዎ እየሰራ መሆኑን ለማረጋገጥ እድል ይሰጥዎታል፣ ከIRB-RPD ሰራተኛ ጋር ግንኝነቱን ያረጋግጡ ፣ እና እርስበርስ እየተግባባቹ እንደሆነ ለማረጋገጥ ከIRB አስተርጓሚ ጋር ይነጋገሩ። አባሉ ችሎቱን ሲቀላቀሉ እርስዎን ያነጋግራሉ እና እርስዎ ብቻዎን እና በግል ቦታ ላይ መሆንዎን እንዲያረጋግጡ ይጠይቁዎታል። በመስመር ላይ ስብሰባ ላይ የማየት ወይም የመስማት ችግር ካጋጠመዎት ለአባላቱ ያሳውቁ።
ምናባዊ ችሎት ካልፈለጉ
ሁሉም የስደተኞች ችሎቶች በምናባዊ ቀጠሮ ይያዝላቸዋል ፣ ግን ወደ በአካል ግንኙነት/ችሎት ሊቀየሩ ይችላሉ።
ይህን ፎርም ሞልተህ ቢያንስ ችሎት ከመሰማቱ በፊት በአስር ቀናት ውስጥ መላክ አለብህ። ለምን በአካል ችሎት እንደሚፈልግዎት ወይም እንደሚፈልጉ መናገር አለቦት።
በአካል ተገኝተው የሚሰሙ ችሎቶች
በአካል ተገኝተው የሚሰማ ችሎት የሚካሄደው በIRB-RPD ቢሮ ውስጥ ነው። ሁሉም ሰው በአንድ ክፍል ውስጥ ይሆናል።
በአካል ችሎት የሚኖርዎት IRB-RPD ችሎትዎ በአካል እንዲታይ ከወሰነ ወይም በአካል ችሎት እንዲታይ ከጠየቁ እና IRB-RPD ከፈቀደ ብቻ ነው።
በአካል ችሎት የሚካሄደው በIRB-RPD ቢሮ ውስጥ ነው። እርስዎ ወይም የህግ ተወካይዎ IRB-RPD ቀን እና ሰዓት ካስቀመጠ በኋላ የመቅረብያ ማሳወቂያ ደብዳቤ ያገኛሉ። የመቅረብያ ማስታወቂያ ችሎትዎ የሚካሄድበትን አድራሻ ይገልፃል። ማስታወቅያው ምን ማድረግ እንዳለብዎት ስለሚገልጽ ማስታወቂያውን በጥንቃቄ ያንብቡ።
በአካል ችሎትዎ ላይ
በአካል ችሎት በሚሰማበት ቀን፣ ቢያንስ ከ15-30 ደቂቃዎች ቀደም ብለው መድረስዎን ያረጋግጡ። ይህ የችሎት ክፍሉን ለማግኘት ጊዜ ይሰጥዎታል። ታዛቢዎች ወይም ምስክሮች ካሉዎት፣ እንዲሁም ከችሎቱ ቢያንስ 15 ደቂቃዎች በፊት ቀደም ብሎ መምጣት አለባቸው። ችሎቱ እስኪዘጋጅ ድረስ በመጠባበቂያ ክፍል ውስጥ እንዲቆዩ ሊጠየቁ ይችላሉ። ችሎቱ ከመጀመሩ በፊት፣ እርስ በርስ መረዳዳትዎን ለማረጋገጥ ከአስተርጓሚው ጋር ይነጋገሩ።
