የኔ የስደተኛ ይገባኛል ጥያቄ ማመልከቻ እንኳን በደህና መጡ (My Refugee Claim)
የእኔ የስደተኛ የይገባኛል ጥያቄ በካናዳ ውስጥ የስደተኛ ጥያቄ ለሚያደርጉ ሰዎች ነው።
የእኔ የስደተኛ ይገባኛል ጥያቄ እርሶን ለመርዳት ሶስት መርጃዎችን ያቀርባል ይህም ድህረ-ገጽ፣ አቅጣጫ መረጃ ሰጪ ቡክለት (Orientation Booklet) እና ዳሰሳ ዝግጁ ጉብኝቶች (Ready Tours) ማለትም በስደተኛ የይገባኛል ጥያቄ ጉዞዎ ሁሉ መረጃ ያገኛሉ፣ ከሚፈልጉት አካል ጋር ይገናኛሉ እና ይዘጋጃሉ።
ይሄን ድህረ ገፅ እንዴት መጠቀም ይቻላል
በካናዳ የስደተኞች ጥበቃ ሂደት ውስጥ የሚያደርጉት ጉዞ የራስዎ ይሆናል። ነገር ግን ሁሉም የስደተኛ ጠያቂዎች መውሰድ ያለባቸው ጠቃሚ እርምጃዎች አሉ። በሂደቱ ውስጥ የት እንዳሉ ለማወቅ፣ ምን ማድረግ እንዳለቦት ለማወቅ እና ለሚመጣው ለመዘጋጀት የዚህን ድህረ ገጽ ስምንቱን ክፍሎች ይጠቀሙ።

የአቅጣጫ መረጃ ሰጪ ቡክለት (Orientation Booklet)
የአቅጣጫ መረጃ ሰጪ ቡክለት ይመልከቱ እና ያትሙ። ይህ ተግባራዊ መገልገያ የካናዳ የስደተኞች ጥበቃ ሂደት አጠቃላይ እይታ ይሰጥዎታል። በጉዞዎ ውስጥ ወደፊት ይጠቀሙበት።
