የ ስደተኝነት ማመልከቻዎን ቀድመው ያስገቡ ቢሆንም እንካን በካናዳ የወጡ ኣዲስ ህጎች የስደተኝነት ማመልከቻዎ ላይ ተፅእኖ ሊኖራቸው ይችላል ። እዚህ ዌብሳይት ላይ የሚገኙ ኣንዳንድ መረጃዎች ቀናቸው ያለፈባቸው ናቸው ። ወቅታዊ እያደረግናቸው እንገኛለን ። ጠበቃዎን ወይምንም የሚታመንን የመልሶ ማቃቃም ኣገልግሎት ኣቅራቢን ያነጋግሩ ። ለተጨማሪ መረጃ

የስደተኝነት ማመልከቻ ብቁነት ላይ ተፅእኖ የሚኖራቸው ኣዲስ ህጎች

ከ መጋቢት 26-2026 ጅምሮ ቢል ሲ -12 ( Bill C-12 ) የተባለ የስደተኝነት ጥያቄ ማመልከቻን የሚመለከት ህግ ተግባራዊ ሆናል ።

ኣዲስ የብቁነት ህጎች

እነዚህ ኣዲስ ህጎች ከ ስኔ 3-2025 ጀምሮ በገቡት ሁሉም ማመልክቻዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናሉ ።

ከሚከተሉት ውስጥ ከሆነ ማመልከቻዎ ወደ ኢሚግረሽን እና ስደተኞች ቦርድ ( IRB ) ለመላክ ብቁ ኣይሆንም ።

  • * ወደ ካናዳ ለመጀመርያ ግዜ ገብተው የስደተኛ ማመልከቻዎን ሳያስገቡ ከኣንድ እመት በላይ ከቆዩ ( ከ ሰኔ 24-2020 ቦሃላ ) ከኣገሪትዎ ወጥተው ተመልሰው የገቡም ቢሆን ።
  • * ወደ ካናዳ ብይፋዊ መተላለፍያ ድንበሮች ገብተው የስደተኝነት ማመልከቻዎን ከገቡበት ቀን ጀምሮ ከ 14 ቀናት በላይ ቆይተው ካቀረቡ*

* የሶስተኛ ደህንነታቸው የተጠበቁ ኣገሮች ስምምነት (STCA) ኣሁንም ስራ ላይ እንደዋለ ነው ። ወደ ካናዳ ብይፋዊ መተላለፍያ ድንበሮች ገብተው በ 14 ቀናት ውስጥ ማመልከቻዎን ኒያስገቡም ፣ ማመልከቻዎ ወደ IRB ለመላክ ብቁ ሆኖ ኣይገኝም ፣ በ STCA ጉዳይዎ በልዩ ሁኔታ እንዲታይ ከተፈቀድልዎ በስተቀር ።

ለተጨማሪ ዘርዘር ያለ የ ብቁነት መረጃ ፣ የ IRCC ድህረ ገፅን ይመልከቱ :

ኣስፈላጊ : IRCC እና CBSA ከ ስኔ 3-2025 ቦሃላ የቀረቡትን ሁሉን ማመልከቻዎች ደግመው እየመረመሩ ነው ። ማመልከቻዎ በዚህ ኣዲስ ህግ የሚመለከተው ከሆነ ፣ እርስዎን እና ህጋዊ ወኪልዎን እናነጋግራለን ። IRB ፣ IRCC ፣ CBSA፣ እና ህጋዊ ወኪልዎ እርስዎ ወቅታዊ የሚገኙበትን መረጃ እንዳላቸው ያረጋግጡ ።

ማመልከቻዎ ወደ IRB ለመቅረብ ብቁ ካልሆነ

የስደተኝነት ማመልከቻዎ ብቁ ካልሆነ ፣ ወደ ካናዳ የድንበር ኣገልግሎት ኤጀንሲ ( CBSA ) ይላካሉ ። CBSA ደግሞ ለቅድመ መንቀሳቀስ ሪስክ ግምገማ ( PRRA) ማመልከት ይችሉ እንደሆነ ይወስናል ።

PRRA ማለት ወደ መጡበት ኣገር ተመልሰው ከተላኩ የደህንነት ስጋት ፣ ስቃይ እና መጥፎ ኣያያዝ ያጋጥመኛል ካሉ ያንን ለመከላከል የሚደረግ ማማመልከቻ ነው ። PRRA እንደ የስደተኛት የመሰማት ችሎት ኣይደለም ።ነገር ግን ተቀባይነት ካገኙ ጥገኝትን ሊያገኙ ይችላሉ ።

ድጋፍ እና መረጃ ማግኘት

  • ስለስደተኝነት ማመልከቻዎ ብቁነት ወይንም ያሳሰብዎት ጥያቄዎች ካለዎት መረጃን ያግኙ ወይንም ከጠበቃዎ ወይም የህግ ተወካይዎ ምክር ያግኙ
  • ።የመልሶ ማቃቃም ድርጅቶች እነዚህን ኣዳዲስ ህጎች ለመረዳት እና ከህግ ተወካዬችዎ/ ጠቃሚ ነገሮች ጋር እንዲገናኙ ይረዳሉ

የነዛን ተቃማትን ዝርዝር ለማግኘት ፣ ይሄንን ይመልከቱ Community Resources