የ ስደተኝነት ማመልከቻዎን ቀድመው ያስገቡ ቢሆንም እንካን በካናዳ የወጡ ኣዲስ ህጎች የስደተኝነት ማመልከቻዎ ላይ ተፅእኖ ሊኖራቸው ይችላል ። እዚህ ዌብሳይት ላይ የሚገኙ ኣንዳንድ መረጃዎች ቀናቸው ያለፈባቸው ናቸው ። ወቅታዊ እያደረግናቸው እንገኛለን ። ጠበቃዎን ወይምንም የሚታመንን የመልሶ ማቃቃም ኣገልግሎት ኣቅራቢን ያነጋግሩ ። ለተጨማሪ መረጃ

የስደተኛ ጥያቄዎ ውድቅ ተደርጓል

ስደተኛ ጥገኝነት ቦርድ ስደተኛ መከላከል ክፍል (IRB-RPD) የይገባኛል ጥያቄዎትን ውድቅ ካደረገው፣ ምክንያቱ ሊሆን ይችላል፡-

  • ጥያቄዎን አያምኑበትም።
  • ማንነትዎን አያምኑበትም።
  • ጥበቃ እንደሚያስፈልግዎት በቂ ምክንያት እንዳልዎት አያስቡም።
  • በአገርዎ ያሉ ባለስልጣናት እርስዎን መጠበቅ እንደሚችሉ ያስባሉ።
  • በአገርዎ ውስጥ ለእርስዎ ለመኖር አስተማማኝ እና ምክንያታዊ የሆነ ቦታ እንዳለ ያስባሉ ።
  • እርስዎ ምንም አደጋ በማይኖርበት የሌላ ሀገር ዜጋ ወይም ቋሚ ነዋሪ ነዎት።
  • በከባድ ወንጀል፣ የጦር ወንጀሎች ወይም በሰው ልጆች ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ተሳትፈዋል።

የይገባኛል ጥያቄዎ ውድቅ ከተደረገ በኋላ አማራጮች

የይገባኛል ጥያቄዎ ውድቅ ከተደረገ፣ በካናዳ ውስጥ ለመቆየት ወይም ቋሚ ነዋሪ ለመሆን አሁንም መንገዶች አሉ። የሚከተሉትን ማድረግ ይችሉ ይሆናል፡-