የ ስደተኝነት ማመልከቻዎን ቀድመው ያስገቡ ቢሆንም እንካን በካናዳ የወጡ ኣዲስ ህጎች የስደተኝነት ማመልከቻዎ ላይ ተፅእኖ ሊኖራቸው ይችላል ። እዚህ ዌብሳይት ላይ የሚገኙ ኣንዳንድ መረጃዎች ቀናቸው ያለፈባቸው ናቸው ። ወቅታዊ እያደረግናቸው እንገኛለን ። ጠበቃዎን ወይንም የሚታመንን የመልሶ ማቃቃም ኣገልግሎት ኣቅራቢን ያነጋግሩ ። ለተጨማሪ መረጃ

ከችሎትዎ በኋላ

ይህ ክፍል ከችሎትዎ በኋላ ስለሚሆነው ነገር ከፍተኛ ደረጃ መረጃ እና ጠቃሚ ምክሮችን ይሰጥዎታል።

አወንታዊም ሆነ አሉታዊ ውሳኔ፣ ለቀጣይ እርምጃዎች ዝርዝር መረጃ በክፍል 7 – ከችሎትዎ በኋላ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ

ውሳኔው

አባሉ ስለ እርስዎ የይገባኛል ጥያቄ በችሎቱ መጨረሻ ላይ ሊወስን ይችላል። ተጨማሪ ጊዜ ከፈለጉ ውሳኔያቸውን በፖስታ እልክዋለሁ ሊሉ ይችላሉ። ይህ አስጨናቂ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ጉዳይዎ  ውድቅ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው ማለት አይደለም።

IRB-RPD የተስጠውን ውሳኔ ማሳወቂያ ማስታወሻ ከነ የውሳኔው ምክንያቶች በፁሑፍ ይልካል።

የህግ ተወካይ ካልዎት የውሳኔው ማሳወቂያ ማስታወሻ በ ማይኬዝ በኩል ወደዛ ይላካል ። ከዛ እነሱ ያጋርዎታል ።

እራሶን የወከሉ እንደሆነ IRB-RPD የውሳኔ ማሳወቂያ ማስታወሻውን በማይኬዝ በኩል ይልክሎታል ። ማይ ኬዝ የሌልዎት እንደሆነ ውሳኔውን በፓስታ ይልክልዎታል ።

ውድቅ ከተደረገቦት

የይገባኛል ጥያቄዎ ውድቅ ከተደረገ ህጋዊ አማራጮች አሉ። የሕግ ተወካይዎን ያነጋግሩ።

ቋሚ ነዋሪ ለመሆን ያመልክቱ

የስደተኛ ጥያቄዎ ተቀባይነት ካገኘ፣ ለቋሚ ነዋሪነት ወዲያውኑ ያመልክቱ። ይህንን ለራስዎ እና ለቤተሰብዎ አባላት ያድርጉ። ከዘገዩ እንደ የስራ ፍቃድ ማደስ ያሉ ችግሮች ሊያጋጥሙዎት ይችላሉ። ያስታውሱ፣ የስደተኛ ጥበቃ ካገኙ፣ ወደ ትውልድ ሀገርዎ መመለስ አይችሉም። እንደዛ ካደረጉ፣ መንግስት የይገባኛል ጥያቄዎን ለሌላ ችሎት ወደ IRB-RPDሊልክ ይችላል።


የሚቀጥለው የመመርያ ክፍል 3 የሕግ ውክልና ያግኙ