የ ስደተኝነት ማመልከቻዎን ቀድመው ያስገቡ ቢሆንም እንካን በካናዳ የወጡ ኣዲስ ህጎች የስደተኝነት ማመልከቻዎ ላይ ተፅእኖ ሊኖራቸው ይችላል ። እዚህ ዌብሳይት ላይ የሚገኙ ኣንዳንድ መረጃዎች ቀናቸው ያለፈባቸው ናቸው ። ወቅታዊ እያደረግናቸው እንገኛለን ። ጠበቃዎን ወይንም የሚታመንን የመልሶ ማቃቃም ኣገልግሎት ኣቅራቢን ያነጋግሩ ። ለተጨማሪ መረጃ

ውሳኔዎን ያግኙ

የካናዳ የኢሚግሬሽን እና የስደተኞች ቦርድ – የስደተኞች ጥበቃ ክፍል (IRB-RPD) የስደተኛ ጥያቄዎ በካናዳ ተቀባይነት ይኖረው እንደሆነ ይወስናል።

በስደተኛ ችሎትዎ መጨረሻ ላይ የቦርዱ አባል የሚከተሉትን ማድረግ ይችላል፡-

  • ችሎቱ በቀጣይ እንዲቀጥል የሚያስፈልግ ከሆነ ይንገርዎታል።
  • የይገባኛል ጥያቄዎ ተቀባይነት ካገኘ ወይም ውድቅ ከተደረገ ይነግርዎታል። ይህ የቃል ውሳኔ ይባላል።
  • ከመሰማት ችሎቱ ቦሃላ ውሳኔውን የህግ ተወካይዎ ይላካል ። ይህ የጽሁፍ ውሳኔ ይባላል።
  • እርስዎ ወይም የህግ ተወካይዎ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ተጨማሪ ሰነዶችን ወይም መረጃዎችን ለመላክ በቂ ጊዜ ይስጣቿል።

የሚቀጥለው የመመርያ ክፍል 7.2 የስደተኛ ጥያቄዎ ተቀባይነት አለው።